የዉድብሪጅ አካባቢ የአንድነት መረዳጃ እድር
መተዳደሪያ ደንብ
በውድብሪጅ ከተማና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች ተቀራራቢ ባህል ያላቸው የህብረተሰብ አባል ከዚህ አለም በሞት ሲለያቸው ለቀብሩ ማስፈጸሚያ የሚወጣው የገንዘብ መጠን ለአንድ ሰው ወይንም ለቤተሰቡ ከአቅም በላይ እየሆነ መጥቶአል፡፡ በተጨማሪም ወገኖቻችን ከባድ ችግር ሲደርስባቸው ለወገን ደራሽ ወገን እንደሆነ እናውቃለን። ይህንን ከፍተኛ ችግር ለማቃለል ይቻል ዘንድ አንድነት የመረዳጃ እድር ቀለል ባለና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ባሳተፈ መልኩ በዚህ ደንብ ውስጥ የተገለጸውን የገንዘብ መጠን በማዋጣት የሟቹን የቀብር ስነ ስርዓት በክብር ለማስፈጸምና ሌሎች ከባድ ችግሮቻችንን ሊያቃልልን ይረዳ ዘንድ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መሠረተ ሃሳቦች ላይ በመመርኮዝ በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት እድሩ ሊቋቋም ችሏል።
ምዕራፍ 1:
ጠቅላላ ድንጋጌ
አንቀጽ 1.1: ስያሜ
1.1.1 ይህ እድር የዉድብሪጅ አካባቢ አንድነት መረዳጃ እድር ተብሎ ይጠራል።
አንቀጽ 1.2: አድራሻና አቋም
1.2.1 የእድሩ አድራሻ በቨርጂኒያ ስቴት ውድብሪጅ ከተማ ነው።
1.2.2 እድሩ በቨርጂኒያ ስቴት ሕግ መሰረት የተቋቋመና ለትርፍ የማይሰራ ድርጅት ነው።
1.2.3 እድሩ የተቋቋመው ላልተወሰነ ጊዜ ነው።
አንቀጽ 1.3: ዓላማ
1.3.1. የእድር አባል ወይም የአባል ቤተሰብ በሞት ሲለይ ለቀብር ስነ – ስርዓት ማስፈጸሚያ ወይም ለአስከሬን መላኪያ የሚሆን የገንዘብ እርዳታ ለማድረግ፣
1.3.2. አባል ወይም የአባል ቤተሰብ ሲሞት የእድሩ አባላት ለቅሶ እንዲደርሱና እንዲያስተዛዝኑ፣ ኢንፎርሜሽን ማዳረስና ማስተባበር፣
1.3.3. የለቅሶ ሥራን ማከፋፈል፣
1.3.4. አባላት የሟችን ቤተሰብ እንዲያጽናኑና በሚይስፈልገው ነገር ሁሉ እዲተባበሩ መንገር፣
1.3.5. ለቀብር አፈጻጸም ወይም ለአስከሬን ማጓጓዝ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ለሟች ቤተሰብ መስጠት፣
1.3.6. ለአባላት ጥቅም ያስገኛል ብሎ የሚያምንበትን ማንኛውንም ዓላማ እንዳስፈላጊነቱ መጨመር
አንቀጽ 1.4: ትርጓሜ
1.4.1 በወንድ ጾታ የተገለጸው ለሴትም ያገለግላል።
1.4.2 እድር ማለት የዉድብሪጅ አካባቢ አንድነት መረዳጃ እድር ማለት ነው።
1.4.3 አባል ማለት የዉድብሪጅ አካባቢ አንድነት መረዳጃ እድር መተዳደሪያን ደንብ ተቀብሎ የተመዘገበ እና የአባልነት ግዳጁን እየፈጸመ ያለ አባል ማለት ነው።
1.4.4 ቤተሰብ ማለት አባል፣የአባል ባለቤት፣ ልጆች ፣ በአባሉ የሚተዳደሩ ሆኖ በአባሉ ቤት የሚኖሩ የአባሉ ወላጆች፣በአባሉ የሚተዳደሩ ሆኖ በአባሉ ቤት የሚኖሩ እድሜያቸው ከ21 አመት በታች ሆነው የአባሉ ወንድምና እህቶች ማለት ነው።
አንቀጽ 1.5: የእድር ገቢ
1.5.1. ከአባልነት ክፍያ፣ አንድ አባል እዲሁም አባል ከነቤተሰቡ (ባልና ሚስት፡ ልጆቻቸው ጋር) በዓመት $360 ዶላር ከሚከፈል፤
1.5.2. በስጦታ ከሚገኝ፤
1.5.3. እድሩ የሚያዘጋጀውን ፕሮግራም ስፓንሰር ከሚያደርጉ ወይም እርዳታ ከሚሰጡ ድርጅቶች የሚገኝ ገቢ ይሆናል።
1.5.4 አመታዊ የመስተንግዶ መዋጮ (ለበጋ የቤተሰብ ፒክኒክ እና ለክረምት ጠቅላላ ጉባኤ): አንቀፅ 2.4.1. ይመልከቱ፡፡
1.5.5 በምዝገባ ወቅት የሚከናወን የምዝገባ ክፍያ: አንቀፅ 2.4.1. ይመልከቱ፡፡
ምዕራፍ
2:
አባልነት
አንቀጽ
2.1:
አባል
ስለመሆን
2.1.1 በቨርጂኒያ ስቴት ውድብሪጅ አካባቢ የሚኖር ዕድሜው 21 እና ከዚያ በላይ የሆነ፣
2.1.2 የእድሩን ደንብና ሕግ የተቀበለ ማንኛውም ሰው አባል መሆን ይችላል።
2.1.3 አባል ከአካባቢው ለቆ በሌላ ቦታ መኖር ከጀመረ ግዴታውን በማክበር በአባልነት መቀጠል ይችላል። አንድ አባል አካባቢውን ለቆ ከሄኤደ በሁአላ ችግር ቢደርስበት በደንቡ መሰረት የገንዘብ እርዳታ ያገኛል, ነገርግን በርቀት ምክንያት አባላት የእራት መስተንግዶ ላያደርጉና የቀብር ስነስርአት ላይ ላይገኙ ይችላሉ።
2.1.4 እድሩ እስከ ሁለት መቶ (200) አባላቶች ይኖሩታል። ነገር ግን ወደፊት ሁኔታዎች ከፈቀዱ እንደአስፈላጊነቱ ይህ ደንብ ሊሻሻል ይችላል።
አንቅጽ 2.2: የአባል መብት፣
2.2.1. አንድ አባል ከተመዘገበ ቀን ጀምሮ የመምረጥ መብት አለው።
2.2.2. አንድ አባል በአባልነት አንድ ዓመት ከሆነው የመመረጥ መብት ይኖረዋል።
2.2.3. አንድ አባል በአባልነት ሙሉ ዓመት ካልሞላው (ጎደሎ ዓምት/ fraction of a year) የገንዘብ ጥቅም አያገኝም። እድሩ ግን እራት ያበላል፡፡
2.2.4. አንድ አባል ከተመዘገበ ቀን ጀምሮ በቤተሰቡ ላይ በአስራ ሁለት ወራት ውስጥ ሞት የደረሰበት ከሆነ፣ እድሩ ለማስተዛዘን እራት ያበላል፣ ለአንድ(1) ቀን ያስተናግዳል፣ ያስተዛዝናል።
2.2.5. ለማስተዛዘንና እራት ለማቅረብ ያልታሰበ ምክኒያት ከተፈጠረ፣ እድሩ ከሟች ቤተሰብ ጋር በመተባበር/ተመካክሮ እራቱን በአመቺ ጊዜ ያቀርባል፡፡ ይህ ድርጊት ሐይማኖታዊ ስነ ሥርዓትን አያጠቃልልም።
2.2.6. አንድ አባል የአባልነት ግዴታውን ከአንድ ዓመት በላይ እያሟላ ከቆየ በኃላ፤ በአባሉ ወይም በባለቤቱ ላይ የሞት አደጋ ሲገጥም፤ አሥር ሺህ ዶላር ($10,000.00) ያገኛል።
2.2.7. አንድ አባል የአባልነት ግዴታውን ከአንድ ዓመት በላይ እያሟላ ከቆየ በኃላ፤ የአባል ልጅ የሞተ እንደሆነ አባል ከሚያገኘው 50% ያገኛል ($5,000.00) ።
2.2.8. አንድ አባል የአባልነት ግዴታውን ከአንድ ዓመት በላይ እያሟላ ከቆየ በኃላ፤ በአባሉ ቤት ተመዝግበው የሚኖሩና አባሉ የሚያስተዳድረው የአባሉ ወላጅ፣ ወንድም ወይም እህት የሞተ ከሆነና እሬሳ ከቤት ከወጣ $3,000 ያገኛል። (አንቀፅ 1.4.4 ይመልከቱ)
2.2.9. አባሉና ባለቤታቸው በህመም ምክንያት አልጋ ላይ ለሁለት ወር ቢቆዩ ሁለቱም አንድ ላይ ከታመሙና ሁለቱም ስራ ከፈቱ $2000 ለሁለቱ ይከፈላል። ሆኖም ግን ለአባላት በህመም ወቅት የሚከፈል ክፍያ ሁለቱም ስራ የፈቱና ደሞዝ የማይቀበሉ መሆኑን በአባላት ሲረጋገጥ ነው። በህመም ምክንያት የተከፈለው አባል እስከ አንድ አመት ድረስ እንደገና ቢታመም ተጨማሪ አይከፈለውም ። አንድ አባል በህመም ምክንያት ሥራ ፈትቶ(ታ) ሦስት ወር ከሆነ አባሎች በመተባበር በጥሬ ገንዘብ ወይም በአይነት ሊረዱት ወይም ሊረዷት ይገባል። የአባሉ ወርሃዊ ክፍያም ሃያ ብር ዝቅ ይደረግለታል። ሥራ ሲጀምር ግን ወደ መደበኛው ክፍያ ይመልሳል ።
2.2.10. ከአንድ በላይ በቤተሰብ ላይ ሞት ቢደርስ፣ የእድሩ ቦርድ አባላትንና ጠቅላላው ጉባኤው የገንዘብ እርዳታ እንዲያደርጉ ይጠይቃል፡፡
2.2.11. ከቨርጂኒያ እስቴት ውጭ አባል ከሞተ፤ ጉዳዩ እስከሚጣራ፣ እድሩ የተጠቃሚ ገንዘብ ክፍያን ያዘገያል፡፡ የሞት ምስክር ወይም ሌላ ሕጋዊ ወረቀት ማረጋገጫ ለመመልከት እድሩ የመጠየቅ መብት አለው፡፡
ማሳሰቢያ፡ አንድ አባል ከጠፋ ወይም የት እንደደረሰ የማይታወቅ ከሆነ፣ አባሉ የተጠቃሚ ክፍያ አያገኝም ፡፡
– ከጥቅም ክፍያ ላይ፡ ያልተከፈሉ ወዝፍ እዳዎች አስቀደመው ይቀነሳሉ፡፡
– የኤሌክትሮኒክ ክፍያ እስከሚጀመር፣ ክፍያ ሁሉ በቸክ ወይም በመኒ ኦርደር ይሆናል፡፡
– ለሕክምና ወይም ለሌላ ምክኒያት፡ እድሩ ቅድመ ክፍያ አያደርግም፡
አንቀጽ 2.3: የአባል ግዴታና መብት
2.3.1
የእድሩ
ደንብ
የሚጠይቀውን
መፈጸም፤
2.3.2
የአባልነትና
ሌሎች
ቅጾችንም
በአግባቡ
በትክክል
ሞልቶ
ለእድሩ
የመስጠት፤
2.3.3
መደበኛ
የአባልነት
መመዝገቢያና
ሌላም
በሞት
ጊዜ
ለሚደረጉ
መዋጮዎች
በወቅቱ
መክፈል፤።
2.3.4
አስገዳጅ
ሁኔታ
ካላጋጠመ
በስተቀር
በጠቅላላ
ስብሰባ
ላይ
መገኘት፤
2.3.5
በአባላት
መካከል
የመግባባትና
የመተባበር
ስሜት
አንዲዳብር
መርዳት፤
2.3.6 አባል ወይም የአባል ቤተሰብ በሞት ከተለየ እያንዳንዱ የእድሩ አባል ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካላጋጠመ በስተቀር፣ለቅሶ መድረስና እዚህ የሚቀበር ከሆነ በቀብሩ ላይ መገኘት፣ አስክሬኑ ወደ አገር ቤት ወይም ሌላ ቦታ የሚሄድ ከሆነም መሸኘት፤
2.3.7 አባል ወይም የአባል ቤተሰብ በሞት ከተለየ፣ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቅ አባል ለእድሩ ተጠሪ ማሳወቅ፤
2.3.8 የአባል ወይም የአባል ቤተሰብ ሁኔታ ከተለወጠ፣ (ለምሳሌ ባልና ሚስት ከተፋቱ፣) ፣ ለውጥ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀናት ውሰጥ ለውጡን ለእድሩ ማሳወቅ ይኖርበታል።
2.3.9 ባልና ሚስት በአንድ ቀን ከተመዘገቡ፤ የአባልነት መብታቸው እኩል ነው፡፡ በምዝገባ ላይ ሁለቱም መገኘት አለባቸው፡፡
2.3.10 አባልና የአባል ባለቤት በተለያየ ጌዜ ከተመዘገቡ፤ የእያንዳዳቸው መብት የሚጀምረው ከተመዘገቡበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡
2.3.11 አባልና የአባል ባለቤት በሕጋዊ መንገድ ከተፋቱ፤ የዉድብሪጅ አካባቢ አንድነት መረዳጃ እድር ማንኛውንም የአባልነት ባለቤትነት ሕጋዊ ውሳኔ ያከብራል፡፡ ሕጋዊ ውሳኔ፣ የባልና የሚስት የግል ስምምነትን በኖተራይዝድ (notarized) ደብዳቤን ያጠቃልላል ( 2.3.8 ይመልከቱ)፡፡ አባል ሁኖ የቀረው፡ የውዝፍ እዳውን ኃላፊነት ይወስዳል፡፡
2.3.12 የተፋታዉ አባል የዓመቱን መዋጮ ብቻ በመክፈል እንደአባል ወዲያውኑ (በተፋቱበት ቀን) ሊቀጥል ይችላል። ካልቀጠለ ግን፡ የሞት አደጋ ቢያጋጥም፤ የተጠቃሚ ክፍያውን ያጣል፡፡
2.3.13 አባል ሲመዘገብ ቅፁ ላይ ተወካዩን ካልገለፀ, የእድሩ አባል ከዚህ አለም በሞት በሚለይበት ጊዜ የሚገባውን የእድር አገልግሎትና ጥቅሞች ባለቤቱ (ቷ) በውክልና ይወስዳል (ትወስዳለች):: ባለቤቱ (ቷ) ከሌሉ ደግሞ በአባልነት ቅፅ ላይ የተመዘገቡት ልጆች ውክልናውን ይወስዳሉ።
አንቀጽ 2.4: የአባልነት መመዝገቢያና ዓመታዊ ከፍያ
2.4.1
የአባነልነት
መመዝገቢያ
|
የአንድ ጊዜ የክፍያ መጠን |
ዓመታዊ የክፍያ መጠን |
እድሩ ሲቋቋም ለገባ ወይም የመስራች አባል የክፍያ ግዴታ |
$200 |
$360.00 |
እድሩ ከተቋቋመ ከአንድ አመት በኋላ ማለትም ከJanuary 15, 2024 ለገባ አባል የክፍያ ግዴታ |
$300 |
$360.00 |
አመታዊ የመስተንግዶ መዋጮ (ለበጋ የቤተሰብ ፒክኒክ እና ለክረምት ጠቅላላ ጉባኤ) |
|
$40 |
2.4.1.1 አንድ ግለሰብ ከአንድ አመት በኋላ ማለትም ከJanuary 15, 2024 እድሩ ውስጥ ለመግባት ቢጠይቅ እና በአንቀጽ 2.1.4 በተጠቀሰው መሠረት የእድሩ አባላት ቁጥር ሁለት መቶ (200) ካልሞላ፣ የአንድ ጊዜ የመመዝግቢያ ክፍያ $300 እና ዓመታዊ የእድር መዋጮ $360 ወይም የግማሽ ዓመት $180 የእድር መዋጮ በመክፈል እድሩን መቀላል ይችላል።
2.4.2 አባል እዲሁም አባል ከነቤተሰቡ (ባል፣ሚስትና አባል የሚያስተዳድራቸው ልጆች ጨምሮ) በየወሩ $30 ዶላር ታስቦ በቅድሚያ በዓመት ሁለት ጊዜ፡ $180.00 (አንድ መቶ ሰማኒያ) ዶላር፣ ወይም በጠቅላላው በዓመት $360.00 (ሶስት መቶ ስልሳ) ዶላር አንድ ጊዜ ይከፍላሉ።
2.4.3 በወረረሽኝ በሽታ ወይም በከፍተኛ አደጋ ምክኒያት፡ የተጠቃሚ ክፍያው እድሩ ካለው ገንዘብ በላይ ከሆነ፣ ጠቅላላ ስብሰባ ተጠርቶ፡ ወይም የእድሩ ቦርድ አባላት በወሰኑት የተጠቃሚ ክፍያ ማስተካከል ይደረጋል፡፡
2.4.4 የእድሩ ተቀማጭ ገንዘብ ከሀያ ሺ ዶላር ($20,000) በታች ከሆነ፤ አባላት ተጨማሪ መዋጮ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ። መዋጮው በአባላቱ በስብሰባ ላይ ይወሰናል፡፡
ም ዕ ራ ፍ 3:
ሥርዓት
አንቀጽ 3.1: የሥነ ሥርዓት እርምጃ
3.1.1 የአባልነት ክፍያ የሚሰበሰበው ዓመቱ ሲጀመር ነው፡፡ አንድ አባል ክፍያውን አላሟላም የሚባለው በወር መክፈል ያለበትን ክፍያ ሳይከፍል ወሩ ካለፈ ወይም በዓመት መክፈል የሚገባውን ክፍያ ሳይከፍል የመክፈያው ዓመት ካለፈ ነው፡፡ የመክፈያው ጊዜ ካለፈ ግን ሃያ አምስት ብር ($25) ይቀጣል፡፡ የአባልነት ክፍያውን ላላሟላ አባል፡ የስልክ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል። አንቀፅ 2.3.3. ይመልከቱ፡፡
3.1.2 አንድ አባል መክፈል የሚገባውን ክፍያ ሳይከፍል የመክፈያው ዓመት 3 ወር (3 month) ካለፈ: በገዛ ፈቃዱ እንደለቀቀ ተቆጥሮ ከአባልነት ይሰናበታል፡፡ የገንዘብ ወይም የእራት ጥቅሙም ይሰረዛል፡፡
3.1.3 አንድ አባል ለረጅም ጊዜ ከአገር (USA) ውጭ የሚቆይ ከሆነ፡ ቅድመ ክፍያ ለዓመታት ሊያደርግ ይችላል፡፡
3.1.4 የአባልነት ግዴታውን ባለመክፈሉ የተሰናበተ አባል እንደ አዲስ ሊመዘገብ ይችላል። የአባልነት መብቱም እንደ ማንኛውም አዲስ አባል ይሆናል።
3.1.5 አንድ አባል የሐሰት መረጃ ለእድሩ ከሰጠና በዚህም የሃሰት መረጃ ምክንያት ሊሰጠው የማይገባውን ገንዘብም ይሁን ሌላ ጥቅም ለማግኘት ጥረት ሲያደርግ ከተገኘ እና ከተረጋገጠ፣ እድሩ አባልነቱን ሊሰርዝ ይችላል። ያገኘውም ጥቅም ካለ፣ እንዲመልስ እድሩ በህግ ይጠይቀዋል።
3.1.5.1 አንድ የእድር አባል ከአባልነት ከተገለለ፣ አባል በነበረበት ወቅት ለእድሩ የከፈለው ማንኛውም ገንዘብ አይመለስለትም።
3.1.5.2 የተገለለውን አባል፣ እድሩ ሁለተኛ ለአባልነት አይቀበለውም፡፡
3.1.6 ሁሉም የእድሩ አባል 10 አባላቶችን በሚያቅፈው የመስተንግዶ ቡድን ዉስጥ መሳተፍ አለበት። አንድ አባል የመስተንግዶ እና የእራት ማብላት ተራ ሲደርሰው በአግባቡ ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል። አንድ ቡድን ተራ ሲደርሰው የእራት ወጪውን ለመሽፈን እንዲያስችል ማህበሩ አስፈላጊውን ወጪ በቅድሚያ ወጪ አድርጎ ለተረኛ አስተናጋጅ ቡድን ኃላፊ በመስጠት መስተንግዶው በአግባቡ እና በፍጥነት እንዲጀመር ያደርጋል።
3.1.6.1 የቡድኑ ኃላፊ የወጪዎቹን ደረሰኝ አሰባስቦ ለገንዝብ ክፍል በማስረከብ ሂሳብ በ 7 ቀን
ውስጥ ማወራረድ ይኖርበታል ።
3.1.6.2 አጠቃላይ የመስተግዶ ወጪው በሂሳብ ክፍሉ ከተጣራ በኋላ ሁሉም የእድሩ አባላቶች
ወጪውን እንዲሸፍኑ ያደርጋል ።
3.1.6.3 አንዴ እራት ያበላ ቡድን በቀጣይ የሚደርሰው የቀሩት ቡድኖች ተራቸዉን አጠናቀዉ ዞሮ ሲደርስ ብቻ ነዉ። ተራው ሆኖ ያለበቂ ምክንያት የመስተንግዶ ቡድኑን ያልተሳተፈ አባል፤ እድሩ ለእራት አውጥቶ ለእያንዳንዱ አባል ከሚደርስበት ገንዘብ ተጨማሪ የ$100 ቅጣት ይከፍላል።
ም ዕ ራ ፍ 4:
የእድሩ የአመራር አካላት
ዕድሩ
ጠቅላላ
ጉባኤ፣
የሥራ
አስፍጻሚና፣
ኦዲተር
ይኖረዋል።
አንቀጽ 4.1: ጠቅላላ ጉባኤ
4.1.1 ጠቅላላ ጉባኤ ማለት የእድሩ አባላት የሚገኙበት ጠቅላላ ስብሰባና የዕድሩ ከፍተኛ የሥልጣን አካል ነው።
4.1.2 ጠቅላላ ጉባኤው በዓመት ሁለት ጊዜ ይጠራል። ሁለትኛው ለሽርሽር (picnic) ነው። ለነዚህ ሁለት ጠቅላላ ጉባዔዎች ወጪ ለመሸፈን እያንዳንዱ የማህርሩ አባል በዓመት ሁለት ጊዜ $20 የማዋጣት ግዴታ አለበት ።
4.1.3 ከግማሽ በላይ አባላት የተገኙበት ጠቅላላ ስብሰባ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል።
4.1.4 ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ምልዓተ ጉባኤ ካልሞላ፣ ተከታይ ሁለተኛ ስብሰባ ጠርቶ የሚገኙ አባላት ከግማሽ በታች ቢሆኑም። ስብሰባው እንደምልዓት ጉባኤ እንደሞላ ይቆጠራል።
4.1.5 ከላይ በአነቀጽ 4.1.3 እና 4.1.4 በተጠቀሰው መሰረት ምልዓተ ጉባኤው በታች በአንቀጽ 4.1.6 የተጠቀሰውን ሳያጨምር ሌላ ማንኛውንም ውሳኔ ማስተላለፍ ይችላል።
4.1.6 እድሩን ለማፍረስ የጠቅላላ ጉባኤው ሁለት ሶስተኛው (2/3) ድምጽ ያስፈልጋል።
4.1.7 እድሩ የፈረሰ እንደሆነ፣ የእድሩ ተንቀሳቃሽና የማይነቀሳቀስ ንብረት፣ ጥሬ ገንዘብ ጭምር በወቅቱ በእድሩ አባል ሆኖ ግዴታቸውን አየተወጡ ላሉ አባላት እንዲሰጥ ይደረጋል።
አንቀጽ 4.2: የጠቅላላ ጉባኤ ተግባርና ሥልጣን
4.2.1 የዳይሬክተሮች ቦርድ ይመርጣል፣
4.2.2 የእድሩን መተዳደሪያ ደንብ ያጸድቃል፣ ያሻሽላል፣
4.2.3 የእድሩን የሥራ ማስኬጃ ወጭ ይፈቅዳል፣
4.2.4 ኦዲተሮችን ይመርጣል፣
4.2.5 የእድሩን ገቢ አሰባሰብ፣ ወጪ አደራረግና ሌሎች የእድሩን የገንዘብ አጠቃቀምና እንቅስቃሴ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣
4.2.6 የቦርዱን ሪፖርት ያዳምጣል፣ ይመረምራል፣ እንደአስፈላጊነቱም መመሪያዎችን ይሰጣል።
አንቀጽ 4.3: የዳሬክተሮች ቦርድ
የእድሩን
ስራ
በቅርብ
እንዲቆጣጠር
በጠቅላላው
ጉባኤ
የሚሰየም
አንድ
የዳሬክተሮች
ቦርድ
ይሰየማል፡፡
ተግባራቱም
የሚከተሉት
ይሆናል፡፡
4.3.1 የቦርድ አባላት ቁጥር አሥራ አንድ ይሆናል፡፡
4.3.2 የቦርዱ አባላት የሥራ ዘመን ሁለት ዓመት ይሆናል። ነገር ግን ባልተጠበቀ ምክኒያት የአባላቱ የሥራ ዘመን እንዲራዘም በጠቅላላ ጉባኤው በድምጽ ብልጫ ከተወሰነ ለሁለት የሥራ ዘመን ሊራዘም ይችላል፡፡
4.3.3 በሁለት የሥራ ዘመናት በተከታታይ ያገለገለ የቦርድ አባል በድጋሚ ለመመረጥ ቢያንስ ለአንድ ዓመት በቦርድ አማካሪነት ማገልገል ይኖርበታል። በቦርድ ስብሰባ ውሳኔ ላይ አይመርጥም፡፡
4.3.4 የቦርዱ አባላት ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልዐተ ጉባኤ ይሆናል።
4.3.5 በማናቸውም የቦርድ ምርጫ ጊዜ ከአባላቱ ከሚቀርቡት ውስጥ የስራ ዘመናቸውን የጨረሱ የቦርድ አባላት ቁጥር ከ50 በመቶ ወይም ከግማሽ ሊበልጥ አይችልም።
4.3.6 አንድ የቦርዱ አባል የሥራ ዘመኑን ሳይጨርስ አገልግሎቱን በማናቸውም ምክንያት ቢያቋርጥ ለቀሪው የሥራ ዘመን ተክቶ የሚያገለግል አባል ቦርዱ ከአባላት መሃል ይሰይማል።
4.3.7 በማናቸውም የቦርድ አባላት ምርጫ ጊዜ የቦርዱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሆነ አባል ተመልሶ ለቦርድ አባልነት ቢመረጥ ቀድሞ ይዞት የነበረውን የስራ አስፈጻሚ ስፍራ መልሶ ሊይዝ አይችልም።
አንቀጽ 4.4 : የዳይሬክተሮች ቦርድ ተግባርና ስልጣን የሚከተሉት ይሆናል።
4.4.1 ከቦርዱ አባላት መካከል ቦርዱ ዘጠኝ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ይመርጣል።
4.4.2 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የእድሩን ስራ ለማካሄድ የሚያወጣቸው የአፈጻጸም ስርዓቶችን ይመረምራል፣ ያጸድቃልም።
4.4.3 የሥራ አፈጻጸም ዘገባ ለጠቅላላ ጉባኤ በተወሰነ ጊዜ ያቀርባል።
4.4.4 የእድሩ ወጪ በጠቅላላ ጉባኤ ከተፈቀደው በላይ አለመሆኑን ይቆጣጠራል፣ ወጪው ከተፈቀደው መጠን ከአስር በመቶ (10%) በላይ ከሆነ ይህ የሆነበትን ምክንያት ለጠቅላል ጉባኤው ያስረዳል።
4.4.5 ማንኛውም የቦርዱ አባል ለእድሩ ለሚሰጠው አገልግሎት ክፍያ ወይም መደጎሚያ አይደረግለትም።
4.4.6 እንደ አስፈላጊነቱ የእድሩ ሊቀመንበር በእድር ጉዳይ ላይ ልምድ ወይም እውቀት ያላቸውን የእድሜ ባለጸጋ ኢትዮጵያውያንን ወይም ከሌላ አገር ይጋብዛል። ሆኖም ግን እነዚህ አማካሪዎች ልምዳቸውን ከማካፈልና ሃሳብ ከመስጠት ውጭ በቦርድ ስብሰባ ላይ ድምጽ አይሰጡም።
4.4.7 የቦርድ ምርጫ በሁለተኛው ዓመት በሚደረግ ስብሰባ ይሆናል፡፡
አንቀጽ 4.5: የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና ኃላፊነት
የሥራ
አስፈጻሚ
ኮሚቴ
፣አንድ
ሊቀመንበር፣
አንድ
ምክትል
ሊቀመንበር፣
አንድ
ፀሃፊ፣
አንድ
አቃቤ
ንዋይ
(
ገንዘብ
ያዥ)፣
ሁለት
የህዝብ
ግንኙነት
ሃላፊ፣
አንድ
የኦፕሬሽንና
የቴክኖሎጂ
ኃላፊና፣
አንድ
የሂሳብ
ባለሙያ
(አካውንታንት)፣
አንድ አስተባባሪ (ኮኦርዲኔተር)
ያሉበት
ባለ
ዘጠኝ
የሥራ
አስፈጻሚ
ኮሚቴ
ያቋቁማል፡፡
ይህ
ኮሚቴም
የሚከተሉት
ተግባራት
ያከናውናል።
4.5.1 የእድሩን የእለተ ከእለት ተግባር የሚያከናውን አንድ ሊቀመንበር፣ አንድ ምክትል ሊቀመንበር፣ አንድ ፀሃፊ፣ አንድ አቃቤ ንዋይ (ገንዘብ ያዥ)፣ይመርጣል፡፡
4.5.2 ለሥራው ክንውን የሚረዱ የስራ አፈጻጸም ስርዓቶች ያሰናዳል። በቦርድ ሲጸድቅም በሥራ ላይ ያውላል።
4.5.3 የዕድሩን ሥራ ለማከናወን አስፈላጊ የሆኑ ንዑሳን ኮሚቴዎች ያቋቁማል፣ መመሪያ ያወጣል፣ መደበኛ ስራውን ያከናውናል።
4.5.4 እንደ አስፈላጊነቱ በየጊዜው እየተገናኘ መደበኛ ስራውን ያከናውናል።
4.5.5 ለቦርዱ የሥራ ክንውን ዘገባ በተወሰነ ጊዜ ያቀርባል።
4.5.6 የእድሩን ገቢ ያሰባስባል።
4.5.7 ቅጾችን አዘጋጅቶ ሥራ ላይ ያውላል።
4.5.8 በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት እርዳታ ይሰጣል።
4.5.9 አስፈላጊ ኢንፎርሜሽን ለአባላት በወቅቱ አንዲደርስ ያደርጋል።
4.5.10 የእድሩን ገንዘብና ንብረት በአግባቡ ይይዛል።
4.5.11 የእድሩ አሠራር የሚሻሻልበት መንገድ እያጠና በቦርድ ሲፈቀድ ስራ ላይ ያውላል።
አንቀጽ 4.6: ሊቀመንበር
4.6.1 የቦርዱን የሥራ አስፈጻሚውን ኮሚቴ ስብሰባ በሊቀ–መንበርነት ይመራል።
4.6.2 የእድሩ ስራ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት አንዲከናወን ያቅዳል፣ የእድሩን ስራ ይመራል፣ አባላትን ያስተባብራል፣ይቆጣጠራል።
4.6.3 የእድሩ ሥራን ይመራል ፡፡ በየጊዜው ለሚደረገው የዳይሬክተሮች ቦርድ ስብሰባን ያስተባብራል፡፡
4.6.4 የሥራ ክንውን ዘገባ በየጌዜው ለሚሰበሰበው ለዳይሬክተሮች ቦርድ ያቀርባል።
4.6.5 የዳይሬክተሮች ቦርድን ስብሰባ ይጠራል፡፡ አስቸኳይ ሁናቴ ካጋጠመው ጠቅላላ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ሃሳብ ያቀርባል።
4.6.6 የወጭ ማዘዣዎችንና ደብዳቤዎችን በዕድሩ ስም ይፈርማል።
አንቀጽ 4.7: ምክትል ሊቀመንበር
4.7.1 ሊቀመንበሩ በማይገኝበት ጊዜ ሊቀመንበሩን ተክቶ የእድሩን ሥራ ያከናውናል።
አንቀጽ 4.8 : ጸሐፊ
4.8.1 የዕድሩን አባላት የስም ዝርዝር ይይዛል።
4.8.2 የቦርዱንና የስራ አስፈጻሚውን ኮሚቴ አጀንዳ አዘጋጅቶ ሊቀመንበሩ ሲፈቅድ በየወሩ የስራ አስፈጻሚው ኮሚቴ አባሎችን፣ በየሶስት ወሩ የባለአደራ ቦርድ አባላትን እንዲሁም በየጊዜው ሲወሰን የእድሩን ሙሉ አባላት ለስብሰባ ይጠራል።
4.8.3 የስብሰባዎችን ቃለጉባኤ ይይዛል፣ ያዘጋጃል፣ ለቦርዱ ያቀርባል።
4.8.4 የእድሩን ጽህፈት ቤት ሥራ ያከናውናል።
አንቀጽ 4.9 : ገንዘብ ያዥ
4.9.1 በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ለእድሩ ገቢ ሊሆን የሚገባውን ገንዘብ በየጊዜው እየሰበሰበ በእድሩ የባንክ ሂሳብ ያስቀምጣል።
4.9.2 በመመሪያው መሰረት ዕድሩ ለአባሎች የሚሰጠውን ዕርዳታ ወይም ክፍያ ቦርዱ ሲወስን ይፈጽማል።
4.9.3 ቼኮች በሁለት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሎች መፈረማቸውን ያረጋግጣል፡፡
4.9.4 የእድሩን ሥራ ማካሄጃ በጀት ያዘጋጃል፣ ሲጸድቅም በሥራ ላይ ያውላል።
4.9.5 ወጪዎቹ በበጀት ከተፈቀደው በላይ አለመሆናቸውን ይከታተላል።
አንቀጽ 4.10: የሂሳብ ሹም (አካውንታንት)
4.10.1 የእድሩን የሂሳብ መዛግብት ይይዛል።
4.10.2 የእድሩን የገቢና የወጪ ደረሰኞች ይይዛል።
4.10.3 ገቢዎች በአግባቡ የተሰበሰቡ መሆኑን መርምሮ ያረጋግጣል።
4.10.4 የባንክ ደብተሮች ይይዛል፣ ያስታርቃል።
4.10.5 የእድሩን ሂሳብ ሪፖርት ያዘጋጃል፣ ያቀርባል።
4.10.6 በመንግስት ተቋማት የሚጠየቅ የሂሳብና የታክስ ሪፖርት ያዘጋጃል።
አንቀጽ 4.11: የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
4.11.1 በማንኛውም እድሩን በሚመለከት ሁኔታ የሚደረገውን የማሰተዋወቅ ሥራ ያከናውናል።
4.11.2 ከተለያዩ ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ይመሰርታል።
4.11.3 እድሩን ለማስተዋወቅና ለማሳደግ የሚረዱ ጽሁፎችን አያዘጋጀ በየቦታው ይበትናል።
4.11.4 ማንኛውንም የዕድሩን ጉዳይ በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃ ለአባላት ያስተላልፋል ወይም መተላለፍን ያረጋግጣል።
4.11.5 የእድሩን ዓላማ ሊያግዝ ከሚችሉ ተቋማት ሊገኝ የሚችለውን ጥቅምና እርዳታ እየተከታተል ለቦርዱ ያቀርባል።
4.11.6 የእድሩን ዓላማ ለማስፈጸም ከሚያግዙ ተቋማት ጋር ግንኙነት በመመስረት ስለዝርዝር ሥራቸው ለቦርዱ ሪፖርት በማቅረብ ዕድሩ በተሻለ ሁኔታ አገልግሎች የሚያገኝበትን መንገድ ያበጃል።
አንቀጽ 4.12: የኦፕሬሽንና ቴክኖሎጂ ኃላፊ
4.12.1 የእድሩ አሠራር በሚቀላጠፍበት ሁኔታ ላይ አጠቃላይ ጥናቶችን እያደረገ ሪፖርቱ ያቀርባል።
4.12.2 ስለ ቀብር ቤቶች፣ትራንስፖርት፣ ፓሊስ፣ እና ሰለመሳሰሉት ከዕድሩ ሥራ ጋር ሰለሚገናኙ ተቋማትና አገልግሎቶች አስፈላጊውን ጥናት እና ክንውን ሪፖርት ለቦርዱ ያቀርባል።
4.12.3 ዕድሩ ከጋራ ዋስትና ወይም መድሕን ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ አጥንቶ ለቦርዱ ሪፖርት ያቀርባል።
4.12.4 የእድሩን ዓላማ ለማስፈጸም ያግዛሉ ተብለው የሚገመቱ ኮሚቴዎችን የማቋቋም ጥረቱን በኃላፊነት ይመራል።
4.12.5 ዕድሩ ሕጋዊ አካል ለማግኘትና ይህን ይዞ ለመቆየት የሚያስፈልገውን ሁኔታ በመከታተል ስራ ላይ ያውላል።
4.12.6 የእድሩን ድህረ–ገጽ የማቋቋሙን፣ የማስተደደሩንና የማሳደጉን ጥረት በኃላፊነት ይመራል።
4.12.7 የዕድሩን የዶመይን (ድህረ ገጽ) ስም ያስመዘግባል፣ ምዝገባውም አንዳያልፍበት በየዓመቱ አስፈላጊውን ዕድሳት ያደርጋል።
4.12.8 አባላት የዕድሩን ድህረ ገጽ በሚገባ የሚጠቀሙበትን ሁኔታ እያጠና ለቦሩድ በማቅረብ ጥናቶችን ስራ ላይ ያውላል።
አንቀጽ 4.13 : አስተባባሪ (ኮኦርዲኔተር)
4.13.1 የመስተንግዶ ቡድኖችን ፈጥሮ በበላይነት ይመራል።
4.13.2 የመስተንግዶ ቡድኖቹን ተራ ወስኖ ይመድባል።
4.13.3 የጠቅላላ ስበሰባዎችን የማስተባበርና የማቀናጀት ሥራ ይሰራል ፡፡
4.13.4 ለእድሩ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በየዓመቱ የሚደረገውን የፒክኒክ ዝግጅት ያስተባብራል።
4.13.5 እድሩ የሚሰጠውን ጥቅማጥቅሞች አባላቱ በአግባቡ እንዲያገኙ ከኮሚቴው ጋር በጣምራ ይሰራል።
አንቀጽ 4.14: ኦዲተር
4.13.1 የዳሬይክተሮች ቦርድ ከጠቅላላ ጉባኤው ውስጥ ሶስት አባላት ያሉበት ኦዲተሮችን ይሰይማል።
4.13.2 የኦዲተሮቹም ተጠሪነት ለቦርዱ ይሆናል።
4.13.3 ኦዲተሮቹም በሂሳብ ባለሙያው ተዘጋጅቶ የቀረበውን ዓመታዊ ሪፓርት መርምረው የደረሱበትን ለቦርዱ ያቀርባሉ።
4.13.4 ቦርዱ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ኦዲተሮቹ ሙሉውን ዓመት የሚያጠቃልል፣ የወራት፣ የሩብ ዓመት፣ ወይም የግማሽ ዓመታት ሪፖርቶችን እንዲያቀርቡ ሊጠይቅ ይችላል።
ምዕራፍ 5:
የእድሩ ሕገ–ደንብ (Bylaw)
5.1 ይህ ሕገ–ደንብ በ2022 የተመሰረተ የዉድብሪጅ አካባቢ አንድነት መረዳጃ እድር ሕገ–ደንብ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል። ከ January 1st, 2023 ጀምሮ በሥራ ላይ ይውላል።
5.2
የዉድብሪጅ
አካባቢ አንድነት
መረዳጃ እድር
አመታዊ
የስራ
አፈፃፀም
እና
የሒሳብ
አያያዝ
በ
January
1st የሚጀምር
ሲሆን
የዓመቱ
ሒሳብ
በ
December
31st ይዘጋል።
(Annual
cycle will be January 1st to December 31st).